ጉብኝት

ስዊድናውያን ላልሆኑ አንባቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ማስታወሻ፡-

ይህ እ.ኤ.አ. 2006 በስዊድን የበጋ ወቅት ስለምናደርገው ጉዞአችን የሚልጽ ዝርዝር ነበር፡፡ ከዚህ በታች ባለው ጽሁፍ ውስጥ በተዘዋዋሪ መንገድ ማስታወቂያችን እንዲህ ብለን በቀላሉ ለማስቀመጥ ሞክረናል፡፡

‹‹ስለ ልጅዎ የወደፊት የፆታ ግንዛቤ ይገድድዎታልን; ከሆነ www.amaso.org ወደሚለው ድረ-ገጽ ይሂዱ››፡፡

ውድ ወላጆችና አያቶች

ከዚህ በታች ያለው ዝርዝር የያዘው በበጋው ወቅት በስዊድን በምናደርገው ጉዞ ልንጎበኛቸው ያቀድናቸውን ከተሞች ያካትታል፡፡ እናንተም ልትጎበኙን ብትመጡ በድረ-ገፃችን የጎን ማውጫ ‹‹አድራሻና ነጻ የሚታደሉ ጽሑፎች›› በሚለው ማገናኛ ውስጥ በዝርዝር የተዘረዘሩትን በነጻ የሚታደሉ ማቴሪያሎችን ትቀበላላችሁ፡፡ በዚህ ድረ-ገጽ በምናቀርበው ጉዳይ ላይ ማናቸውም ጥያቄ ቢኖራችሁ ከዚህ በታች በተዘረዘረው የጉብኝት ቦታዎች ከተጠቀሱት ከተሞች ወደ አንዱ ብትመጡ ደስ ይለናል፡፡ ስለሆነም በላይዋ ላይ በትልቁ www.amaso.org የሚል የተለጠፈ ጽሑፍ ያለባትን አንድ ትልቅ ቀይ ሚኒ ባስ መኪና ይፈልጉ፡፡


አንድ ነገር ልብ በሉ፡፡ ምግብ ለመብላትም ሆነ ነዳጅ ለመቅዳት በቆምንበት ስፍራ ሁሉ በነጻ የሚታደሉትን ወረቀቶች ማደል አንችልም፡፡ ነገር ግን እርስዎን ልናገኝበት ወደምንችል ቀረብ ወደሚል አንድ ቦታ መጥተን ማቴሪያሎቹን እንሰጥዎታለን ጥያቄም ካለዎት መልሳችን ለመስጠት እንሞክራለን፡፡ በድረ-ገጻችን ላይ ሆነው የሚፈልጓቸውን ጽሑፎች ሲጠይቁን በፖስታ ቤት ልንልክልዎ እንችላለን፡፡ አንዳንድ ሰዎች አድራሻቸውን መስጠት አይፈልጉም ስለሆነም ስማቸው ሳይታወቅ ማቴሪያሉን ሊወስዱ ይፈልጋሉ፡፡ ለእነርሱም ቢሆን ይቻላል፡፡

በአካባቢው ባሉ ጋዜጦች ላይ የማስተዋወቅ ሥራ እንሠራን፡፡ እሰካሁን ድረስ ከ14ቱ የአካባቢ ጋዜጦች ውስጥ ሁለቱ /ማለትም ቦሁስላኒንገንና ኖርኪስ አልሃንዳ/ የማስታወቂያ ስራችን ሰርዘውብናል፡፡ ማብራራያ እንዲሰጡኝ የቦሁስለኒንገን አዘጋጆችን ለማግኘት ሞክሬ ግን አልቻልሁም፡፡ በሌላ በኩል ግን የኔርከስ አሌሃንዳ ዋና አዘጋጅ /ኡልፍ ካንደርሰን/ ጽሑፎቻችንን ተመልክቶ ‹‹በተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች (ፒዩፕል ግሩፕስ) ላይ ጥቃትን የሚጭሩ›› ብሎአቸዋል፡፡ የድርጅቱን አፈ-ቀላጤ እነዚህን ሁለቱን የአኗኗር ዘይቤዎች ትንታኔ መድልዎ ያለባቸውና ስለ አንደኛውም ቢሆን በጎ ነገር የማይናገሩ አድርጎ ለምን እንደቈጠራቸው ጠይቄዋለሁ፡፡ ይህንን ለምን አለ ብዬ ሳስብ የግብረ ሰዶማዊነትን የአኗኗር ዘይቤ የሚመርጥ ይመስለኛል፡፡

በጉዳዩ ላይ የኔ አስተያየት እንደሚከተለው ነው፡-

ከራሱ ከአር. ኤፍ. ኤስ. ኤል. ድረ-ገጽ ላይ በተወሰዱ ማቴሪያሎችና የምርምር ሪፖርቶች የተደገፈና እውነተኛ መግለጫ የተሰጠበት የአኗኗር ዘይቤ እንዴት ተደርጎ ነው ‹‹በተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጥቃትን የሚጭሩ›› ተብሎ የሚቆጠረው ;

ኔርከስ አልሃንዳዎች በእርግጥ እንዲህ የሚያምኑ ከሆኑ የስዊድን ሕግ እንደጣስሁ አድርገው ለፖሊስ ሪፖርት ሊያደርጉ ይገባቸው ነበር፡፡

ነገር ግን የዚህን ድረ-ገጽ ይዘቶች ለራሳችሁ ብታነቧቸው፣ አብዛኛዎቹ በልጅነታቸው አስደንጋጭ ገጠመኞችን ካዩባቸው ቤቶች ስለመጡ በምትኩ ለእነዚህ ምስኪን ልጆች ርኅራኄ እንዲፈጥርባችሁ የሚያደርግ ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ የወንድነት ፆታዊ ግንዛቤ እያዳበሩ እንዲሄዱ የሚረዳ አባት ወይም ሞዴል ሊሆን የሚችል ሌላ ወንድ ማጣት በእርግጥም እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ወላጆችና አያቶች ልጆቻቻው ሆኑ የልጅ ልጆቻቸውን ከእንደዚህ መሰሉ አስተዳደግ እንዲታደጉ ግንዛቤው ሊኖራቸው የግድ ነው፡፡ ይህንን መሰል እጅግ አስፈላጊ ዘገባ ለሚያገለግሏቸው ሰዎች መከልከላቸው በኔ አስተያየት የሚስተር አንደርስን ከፍተኛ የሆነ ኀላፊነትን የማጉደል ድርጊት ይመስለኛል፡፡

 አር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. በኔርከስ አሌሃንዳ ጋዜጣ ላይ ድረ-ገጻቸው ለማስተዋወቅ ቢጠይቃቸው ኖሮ ሚ/ር አንደሰን የሚሰጡት መልስ የሚያስገርም ሊሆን እንደሚችል ማንም መገመት ይችላል፡፡ ለመሆኑ ሚ/ር አንደርሰን የማስታወቂያ ሥራውን ይከለክሉ ይሆን አላምንም፡፡ እነርሱም ቢሆኑ በድረ-ገጻቸው ላይ ከሌሎች ነገሮች ተጨማሪ በሕግ የተከለከሉ መድኃኒቶችን ስለ መጠቀም የማስተዋወቅ ሥራ ሠርተዋል፡፡ ልብ በሉ! ከመንግሥት ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ በገፍ የሚፈስለት ድርጅት በድረ-ገጹ ላይ በሕግ የተከለከሉ እጾችን ስለ መጠቀም ደግፎ መጻፉ ያስገርማል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ እብደት እጅግ ከሚገባው ርቀት በላይ እንደሄደ የሚያምን ሰው እኔ ብቻ እሆንን; በእርግጥ ይኽ ሁሉ ነገር ተመልሶ በዲሞክራቲክ አገራችን ውስጥ ያለውን የመናገር ና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነታችን ላይ ጥያቄ ያስነሳል፡፡