ከስዊድን ጕዞ ማስታወሻችን የተወሰደ አጭር ዘገባ

መልእክቶቹ በጊዜ ቅደም ተከተል መሰረት አልተቀመጡም፡፡

ለወዳጆቻችን ከጻፍናቸው ኢ-ሜይል መልእክቶች ዝርዝር ውስጥ የተወሰደ


ሆሞሎቢ ወይስ ሆሞማፊያ

ረቡዕ መስከረም 13 ቀን 2006

ከአንድ ሳምንት ገደማ መልካም የተረጋጋ የስራ ክንዋኔና በተወዳጅዋ ስዊድን የመኪና ጉዞአችን በኋላ ነገሩ እንደገና ተደገመ፡፡ ያሁኑ ጊዜ ገጠመኝ ደግሞ የተለየ አይነት ነበር፡፡ የተለየ የሚያደርገው ነገር ጉዳት ያደረሰብን ሰው ጋር አልተጋፈጥንም፡፡ የሄልሲንቦሪን ነዳጅ ጣቢያ ለቅቀን ለመሄድ መኪናችን ውስጥ ቁጭ ብለን ነበር፡፡ በድንገት የመኪናችን የኋላው መስተዋት በታላቅ ፍዳታ እንክትክት አለ፡፡ እርስ በርሳችን ከተያየን በኋላ በተሰበረው መስኮት ወደ ኋላ ዘወር ብዬ ስመለከት ጀርባውን ሰጥቶን በፍጥነት የሚሸሽ ሰው አየሁ፡፡ በነዳጅ ማደያው ጣቢያ ያሉ ሌሎች ሰዎችም አይተውታል፡፡ ሁሉ ነገር በፍጥነት የተደረገ ስለነበር ሰውዬው ጠፋ፡፡ እንዲያው ዋጋ ከፍሎ ማለትም ቆስሎም ቢሆን የመኪናውን መስተዋት የሰበረውን እብድ ለማያዝ የደፈረ አንድም ሰው አልነበረም፡

 http://www.emaso.org/pictures/clip_clip_image002.jpg 

የተፈጠረው አጋጣሚ ግን ይህንን ጉዞ ለማቆም እንድወስን ገፋፋኝ፡፡ በዚህ ጊዜ 6 ኢንች ስፋት ያለው ትልቅ ድንጋይ በመኪናው የኋላ ወንበር በኩል በኃይል ተወረወረ፡፡ መስኮቶቹ ተሰባብረው ከኋላ ወንበሮች በአንዱ የራስ መደገፊያው ላይ ነጥሮ በመመለሱ ፊት ወንበር ላይ የተቀመጥነውን ማናችንንም ቢሆን አላገኘንም፡፡ አሁን የተወረወረብን ድንጋይ ነው የሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ ጥይት ሊሆን ይችላል ማን ያውቃል; ከጉዞአችን በፊት በኡሜ ከደረሰብን ጥቃት በኋላ ከላንድስክሮና ‹‹ሚሊተርላሬት›› የገዛነውን ና በተከታታይ የለበስነው ጥይት-መከላከያ ሰደርያቸንም ሆነ የመኪናችን መስኮቶችም ጥይትን የማስቀረት አቅም የላቸውም፡፡ / ነሃሴ ( ኦገስት) 29 በሚለው ቀን ስር የተጠቀሰውን ይመልከቱ፡፡ የባለቤቴ አካላዊ ደህንነት ጠባቂ እኔ በመሆኔ ምንም ስንኳን እርሷ እንድንቀጥል ብትሻም ይህ ጉዞ በቂ እንደሆነ ወሰንሁ፡፡ በእስኮነ ግዛት ካሉት ከተሞች ቀሪዎቹን ስድስቱን ልናጣቸው እንችላለን፡፡ በሴፕቴምበር 5 ሌንሸፒንግ ከተማ ከደረሰብን ጥቃት በኋላ ቀጥሎ ሊደርሱ ከሚችሉ የጥቃት ሙከራዎች ለመከላከል በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የፖሊስ መኪናዎች ከጀርባችን ያጅቡን እንደነበር አውቀናል፡፡ በሌላ ሁለተኛ ሰው እንደተረጋገጠልን ከሆነ በእስኮቭደ ከተማም ለዚሁ ዓላማ ብለው በዚያው እንደነበሩ አውቀናል፡፡ ለዚህ ጥበቃቸውም ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ሆኖም ግን ከዚህ በበለጠ ሊሠሩት የሚችሉት ብዙ ነገር ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በውስጣችን የሚብላላው የተጋፈጥነው በስዊድን አገር ካለ አደገኛ የግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች ድርጅት ጋር ይሆንን የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ የአር.ኤፍ.ኤስ.ኤል (RFSL) ሊቀመንበር ሶሪን አንደርሰን በ‹‹ዶገን›› /የስዊድን ዕለታዊ ጋዜጣ/ ላይ በገለጹት ቃል ‹‹አንድ ሰው በውስጡ ይህንን ያህል ጥላቻ ይዞ መጓዙ በጣም ያስደነግጣል›› ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የአር.ኤፍ.ኤስ.ኤል ድርጅት በኛ ላይ ከሚያደርሰው ጥቃት ራሱን ማራቁን ( የሚደገፍ ነገር ነው ) ቢናገሩም አነጋገራቸው የአመጽ ድርጊትን መቃወማቸውን ደካማ ያደርገዋል (በጣምም የማይደገፍ ድርጊት ነው) ፡፡ ጥቂት ሰዎች ለሚወስዱት ሕገ-ወጥ ድርጊት ሁሉ አር.ኤፍ.ኤስ.ኤል ተጠያቂነት እንደሌለበት ሁሉ፣ አር.ኤፍ.ኤስ.ኤልን የሚጠሉ ሰዎች በግብረ ሰዶማውያን ላይ ስለሚሠነዘረው ሕጋዊ ያልሆነ ድርጊት ሁሉ ተጠያቂነት እንደሌላቸው እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን በሁሉም ወገን በአመራር ላይ ያሉ ሰዎች በአመጽ፣ በሽብር ማነሳሳትና በማስፈራሪያ ዛቻዎች ላይ ጠንካራ አቋም ሊወስዱ ይገባል፡፡ በእርግጥ የትኛውም ድርጅት የአባሎቹን የትኛውንም ድርጊት ላይ ተጽእኖ ማሳደር አይችልም፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ግን ተጽዕኖ ማሳደር ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ያህል አር.ኤፍ.ኤስ.ኤል ድርጅት በስቶኮልም በየዓመቱ በሚደረገው ‹‹ የፕራይድ ፌስቲቫል›› ትእይንት ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ለመገመት በቂ ምክንያት አለ ፡፡ በፌስቲቫሉ ላይ ለጉብኝት የመጡ ሰዎች ግብረ ሰዶማዊነትን በሚፈሩት በኡልፍ ኤክማ ፣ በአልፍ ስቬንስንና በጳጳሱ ፎቶግራፎች ላይ የዳርት ቀስት የወረውሩበትን ሁኔታ እየተመለከተ አር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. እንዲህ ዓይነት ነገር እንዲደረግ እንዴት ፈቀደ; ይህ ድርጊት ሰዎች ለሽብር እንዲነሳሱ ማድረግ ካልሆነ በስተቀር ምን ሊባል ይችላል; ጳጳሱስ እሺ በቋሚነት ለአካላዊ ደህንነቱ ጥበቃ ይደረግለታል፣ ግን እንዲህ ዓይነቱ ድጋፍ የሌላቸው ሌሎቹ ወገኖች ምን ተሰምቷቸው ይሆን?

ሚስተር አንደርሰንና አር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. (RFSL) ሊያውቁት የሚገባ ነገር ቢኖር ነጻና ግልጥ በሆነ በዚህ ኅብረተሰብ ውስጥ ወላጆች 1/ በልጆቻቸው ውስጥ ወደፊት የሚፈጠረውን የግብረ ሰዶማዊነት ዝንባሌን እንዴት መከላከል እንደሚገባቸው ለማወቅ ከፈለጉ 2/ ግብረ ሰዶማዊነት በተፈጥሮ የሚመጣ ያለመሆኑን /ጄኔቲክ ያለመሆኑን/ 3/ በአር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. በራሱ በኩል በሚተላለፉና በሌሎች በታወቁ የእስታቲስቲክስ ውስጥ ዘገባዎች የተዘረዘረውን የግብረ ሰዶማዊነት ኑሮ ዓይነትን የሚገልጸውን ዘገባ እንዳያገኙ ሊከለክሉ የሚችሉበት አንዳችም መንገድ ያለመኖሩን ነው፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ ወላጆች ለልጆቻቸው የወደፊቱ የተሻለ ፆታዊ ግንዛቤ እንዲያውቁ የሚረዳቸው በቂ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲወስኑ ይችላሉ፡፡

በአካባቢው ካሉ 42 የጋዜጣ አሳታሚዎች ለድርጅታችን የድረ-ገጽ የማስተዋወቅ ሥራ ለመሥራት ጠይቀን 28ቱ ፈቃደኛ ሆነው ሲበቀሉን 14ቱ ግን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ ነገሩ በማነጻጻር ሲታይ ከተጠየቁት ከሁለቱ አንደኛው አልተቀበልም ነበር ማለት ነው፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተቀባይነት ማግኘታችን አስደንቆናል፡፡ እንዲህ ሊሆን የቻለው የማስተዋወቁ ሥራችንን ፈጽሞ በሦስቱ የከተማው ዋና ዋና አካባቢዎች ባለማድረጋችን ና የገጠሩ ነዋሪ ‹‹ፖለቲካዊ ትክክለኛነት›› /ፖለቲካዊ ኮሬክትነስ/ በሚል ሐሳብ እንደ ተጠፈነጉት በከተማ እንዳሉት የመገናኛ ብዙኃን ሰዎች ስላልሆነ ሊሆን ይችላል፡፡ የተቀባይነቱ መጠን በመጀመሪያው ከፍተኛ በስተመጨረሻ ግን አናሳ ነበር፡፡ ይህንንም ሊሆን የቻለው የግብረ ሰዶማዊነት አቀንቃኝ ድርጅት /ሆሞሎቢ/ ጋዜጦች የኛን ማስታወቂያ እንዳይቀበሉ እየጨመረ ከመጣው ከፍተኛ ጫና የተነሣ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደተጠበቀውም አንዳንድ ጋዜጦች ስላወጡት ማስታወቂያ ወቀሳ ደርሶባቸዋል፡፡ ኒያ ወርምላንድስቲዲንገ የተባለው ጋዜጣ ሰዎች የተለያየ አመለካከታቸውን ሊገልጡ ይገባል በሚል አቋም ማስታወቂያውን ማውጣቱ ተገቢ እንደሆነ ተቃዋሚዎችንም ጠንክሮ እንደተጋፈጠ ለማወቅ ችለናል፡፡ ሌሎች ጋዜጦች ግን ጫናውን ፈርተው ዝም ብለዋል፡፡ ሁለቱ ጋዜጦች ደግሞ ማስታወቂያውን ሁለት ጊዜ ካወጡ በኋላ በተሠነዘረባቸው ትችት ምክንያት ማስተዋወቁን ሠርዘውታል፡፡

በማጠቃለያ ላይ በስዊድን ውስጥ በተዘዋወርንባቸው ጊዜያት ላገኘናቸው ተወዳጅ ሰዎች ሁሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ስላደረግነውና ስላልነው ነገር ሁሉ ጥያቄዎችን ለጠየቁንና እንዲሁም ድጋፍ ላደረጉንልን ና በግንባር ፣ በስልክ፣ እንዲሁም በድረ-ገጽ ላይና በኢ-ሜይል ያገኘናቸውን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡ ስለ ሁላችሁም ( ያላአግባብም ለተቹን ሁሉ) በጎና ቀና አመለካከት በልባችን እንዳለ ብቻ እንገልጻለን፡፡

ማክሰኞ መስከረም 5 ቀን 2006 ተጨማሪ ጥቃቶች

ዛሬ ቀትር ላይ በሲንሾፒንግ ከተማ ደርሰናል፡፡ በዚህ ከተማ ለስዊድን አየር ኃይል አገልግሎት የሚውሉ ተዋጊ አውሮፕላኖች የሚፈበረኩበት ቦታ ነው፡፡ 9 ሚሊዮን ገደማ የሚገመት ሕዝብ ያላት ስዊድን በአለም ካሉ የጦር ተዋጊ አውሮፕላኖች አምራች ተፈላጊ ጥቂት አገሮች ውስጥ አንዷ ናት፡፡ እዚህም የገጠመን ነገር ተመሳሳይ ነው፡፡ ገና በመኪና ማቆሚያ መኪናችን ለማቆምና የሚበላ ነገር ፍለጋ ወደ ፈጣን ምግብ ማቅረቢያ ቦታ ልንሄድ ስንል ድንገት የተወሰኑ ሰዎች ክብብ አድርገው ሊያስፈራሩን ጀመሩ፡፡ እንዲያውም እስከ ምግብ ቤት ተከትለው እስከሚቻላቸው ድረስ በመጮህና በመደንፋት ይህ ነው የማይባል አፀያፊ ስድብ በኔና በባለቤቴ ላይ ያወርዱብን ነበር፡፡ ሌሎቹ ደግሞ መኪናችንን ለሁሉም በምትታይበት ና በቆመችበት ስብርብሯን አወጧት፡ ጠባቂዎች ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ግራ ገብቷቸው ነበር፡፡ ከገባንበት ሬስቶራንስ ደግሞ ወጥተው ሲሄዱ መኪናችንን የሚሰባብሩትን ሰዎች ፎቶ ማንሳት ጀመርሁ፡፡ ቀጥለውም ወደኛ ወጡ አሁን ደግሞ ጥቃቱ በኛ በራሳችን ላይ ያነጣጠረ ነበር፡፡ ለነገሩ በጠባብ የመተላለፊ መንገድ ላይ ሆኖ ሁኔታውን ይከታተል የነበረ አንድ ሰው ፖሊስ ጠርቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ፖሊሶቹ ሲደርሱ ጠብ የፈጠሩት ሰዎች ባንድ ጊዜ ጠፉ፡፡ ፖሊሶቹም ለተፈጠረው ሕገ-ወጥ ድርጊት ማስረጃ ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ አልሳካ ሲላቸው ስለ ሁኔታው ሪፖርት ብቻ መጻፋቸውን ነግረውናል፡፡ እኛም ከመተባበር ሌላ የምናደርገው ነገር አልነበረም፡፡ ሁላችንም ቢሆን ሕግና ሥርዓት እንዲከበር ከባለስልጣናት ጋር ልንተባባር ይገባናል፡፡ እየሆነ የነበረውን ነገር በመመልከቱ ደውሎ ፖሊስ የጠራውን ያንን ሰው እናመሰግነዋለን፡፡ ባስፈራሩንና መኪናችንን በሰባበሩ ሰዎች ላይ ክስ መመስረት ፈጽሞ አልፈለግንም፡፡ በልባችን በእውነት የምንራራላቸውና የምንችለው ነገር ካለ ልንረዳቸው የምናስብላቸው እነዚህ ሰዎች ናቸው፡፡

.http://www.emaso.org/pictures/clip_clip_image004.jpg

ግብረ ሰዶማዊነትን የሚደግፉ ሰዎች (ሆሞሎቢ) መኪናችን ከሰባበሩ በኋላ እኔ ፎቶግራፍ ማንሳት ስጀምር ወዲያው ሸሹና ተጨማሪ ጥቃት ለማድረስ ተመልሰው መጡ፡፡

የስዊድን ጉዞአችንን ወደ ማገባደድ ስንደርስ ከሊንሾፒንግ ከተማ የሚከተለው የኢ-ሜይል መልእክት ደረሰን፡

‹‹የትክክለኛ መልእክቱ ትርጕም››

ይህንን ፕሮፓጋንዳችሁን ማስፋፋታችሁን እስከቀጠላችሁ ድረስ ወደዚህ አካባቢ ድርሽ እንዳትሉ ሁኔታውን እንከታታላላን፡፡ ነገር ግን እንዲህ ካደረጋችሁ ከዚህ አስጠሊታ ውግዝ-ክርስቲያን ፈንዳሜንታሊሰት አስተሳሰባችሁ ጋር ሞት እንደሚገባችሁ ልትቆጥሩ ይገባችኋል፡፡ እንደምንገናኝ ተስፋ አርጋለሁ፡፡›› /ኤ.ኤፍ.ኤ. ሊንሾፒንግ/

የዚህ ጉዞ ዓላማ ወላጆችን ለታናናሽ ልጆቻቸው የተባእት ፆታቸውን /ማስኩሊኒቲ/ እንዲያጎለብቱ፣ የግብረ ሰዶማዊነት ሕይወትን ውስጣቸው እንዳይገባ እንዴት እንደሚከላከሉና ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለማስገንዘብ እነርሱን ለመድረስ ነው፡፡ ስለ ታናናሽ ልጆቻቸው የወደፊት ሁኔታ ትኵረት ሊያደርጉ የሚፈልጉ ጥቂት ሰዎች ያሉ ይመስለናል፡፡ ግብረ ሰዶማውያን ግን በሌሎቹ ሁሉ ላይ ጫና ማሳደር የሚችሉበት ሁሉም ዓይነት ሃይል ማለትም /የመገናኛ ብዙኃን፣ የፖለቲካ፣ የገንዘብና የማስፈራራት/ አላቸው፡፡ በእርግጥም ጠንካራ ድምፆች አሏቸው፡፡ ግን ዛሬ በመካከላችን ያሉትን የአሁኑና የሚመጣው ዘመን ትውልዶች የሆኑትን ልጆች ፆታዊ ግንዛቤ ግራ መጋባት ላይ እንዳይወድቁ ለመርዳት በጎናቸው የሚቆሙ አዋቂዎች ቁጥር በጣም ጥቂት ነው፡፡ የስዊድን ፓርላማ /ሪሽንግ/ ግብረ ሰዶማውያን የጉዲፈቻ ልጆችን ማሳደግ ይችላሉ ብሎ ከፍተኛ ድምፅ እንደሰጠበት ና እንዲህ ዓይነቱ አቋም የተገለጠበት እንደ ጁን 5 ቀን 2005 እ.ኤ.አ. ዓይነት ቀን ከቶ የለም፡፡ /በድረ - ገጹ አፈታሪክ 2 ነጥብ 4 ‹‹የሐፍረት ሰልፍ - ዘ ፓሬድ ኦፍ ሼም/ ይመልከቱ፡፡

ያም ሆነ ይህ ከፖሊስ ጋር ከተነጋገርን በኋላ በትዕግሥት ቆመው ይጠብቁ ለነበሩ ሦስት ወላጆች የሚነበቡ ጽሑፎችን ሰጠን፡፡ የሚያስጨንቀን ግን እነዚህን ጥቃት የሚያደርሱብንን ሰዎች በማየት ፈርተው ወደኛ ለመምጣት የማይፈልጉ ወላጆች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ያለማወቃችን ነው፡፡ በመጨረሻ ለመሄድ ስንነሣ አንድ ደግ ፖሊስ ‹‹የተሰባበረች መኪናችንን በፕላስተር ለጣጥፈን›› ብንሄድ የመኪና ጉዞአችን ሁኔታ ህጋዊ እንደሚሆንል ነገረን፡፡ እኛ ወደ ሊንሾፒንግ ከተማ ከመድረሳችን በፊት ባለው የሳምንቱ መጨረሻ በከተማይቱ ውስጥ በግብረ ሰዶማውያን ተዘጋጅቶ በነበረው የፍቅር ሠልፍ ‹‹ላቭ ፓሬድ›› ጊዜ በኒዮ-ናዚዎችና በግብረ ሰዶማውያን ወንዶች መካከል ግጭት ተነስቶ ነበር፡፡ ከሁለቱም ወገኖች የተሳተፉ ሰዎች ሁሉ ታስረው ነበር ግን ደግሞ ወዲያው ተፈትተዋል፡፡ ከሌሎች አገሮች የመጡ ስደተኞችም በዚሁ በግብረ ሰዶማውያን ሠልፍ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘው ነበር፡፡ ግን አር.ኤፍ.ኤስ.ኤል ተጋባዥ ስደተኞቹ በሠልፉ ባለመሳተፋቸው ቅሬታውን ገልጿል፡፡ ይህ ደግሞ በአሜሪካ አገር ያሉ ግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች ከጥቁር የሰብአዊ መብት እንቀቅስቃሴ ጋር ተባብረው የሚሰሩ መሆናቸውን ለማሳየት የተጠቀመበት ዓይነት ዘዴ ሲሆን ነገር ግን ተቀባይነትን አላገኙም፡፡

እሁድ ሴፕቴምበር /መስከረም/ 3 ቀን 2006 በግብረሰዶም ደጋዎች ( ሆሞሎቢ) የተደረገ ተጨማሪ ጥቃት

ዛሬ ደግሞ በቀትር ጊዜ በስቶኮልም ከተማ የሚገኘውን የንጉሡን ቤተ መንግሥት እየጎበኘን ነበር፡፡ ያኔ የቤተ መንግሥቱ ዘበኞች የሥራ ሰዓት ለውጥ ጊዜ ስለነበር ወታደራዊ የሰልፍ ሥነ ሥርዓት ይደረግ ነበር፡፡ ባለቤቴ አንድ ወጣት ወንድ ልጅ ይከተለን እንደ ነበር አስተዋለች፡፡ ይህ ወጣት ስልክ ደውሎ ጥቂት ተቃዋሚዎችን ማሰባሰብ በመቻሉ እነዚሁ ተቃዋሚዎች በቤተ መንግሥቱ ምድር ቤት ውስጥ በነበረን የትኛውም እንቅስቃሴ ይከታተሉን ጀመር፡፡ የትም ቢሆን ከኛ በኋላ በጥቂት እርምጃዎች ርቀት ላይ ነበሩ፡፡ ከእነርሱ አንዱ በቀይ ቀለም የተጻፉ ‹‹የግብረ ሰዶማዊነት ድርጊቶችን ሁሉ ለማድረግ የሚደፍር›› /ዴር ቱ ኢንጌጅ ኢን ሆሞ ሴክሹዋል አክትስ/ የሚሉ ቃላት በለበሰው ቲ-ሸርት ላይ ተጽፈዋል፡፡ ከእነርሱ መሸሽ ፈጽሞ ያመቻላችን ስገነዘብ ሌላ አደጋ ውስጥ እንዳለን በውስጤ ተሰማኝ፡፡ እኛ አሁን ከሕዝቡ ጋር እስካለን ድረስ ምንም አይደል ነገር ግን መኪናችንን ያቆምነው እዚያው ቤተ መንግሥቱ ግቢ ውስጥ ዘወር ባለ ቦታ ነው፡፡ ታዲያ አንድ ሰው መኪናዬን ሊሰባብራት እንደሚችል አሳሰበኝ፡፡ ጥቃት ሊያደርሱብን የተዘጋጁትን ሰዎች እየጠቆምሁት አጠገቤ ያለውን የፀጥታ አስከባሪ ጉዳት እንዳይደርስብን እስከ መኪናችን ድረስ ሊሸኘን ጠየቅሁት፡፡ እርሱም ሌላ የፀጥታ ሠራተኛ እንድንጠይቅ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሌላ ክፍል ላከን ግን እዚያም አንድም የፀጥታ ሠራተኛ የለም፡፡ ወደ መጀመሪያው ያነጋገርነው የፀጥታ አስከባሪ ፖሊስ ስንመለስ እነዚያው ጥቃት ሊያደርሱብን የተዘጋጁት ግብረ ሰዶማውያን ወንዶች /ጌይ/ እየተከሉን መሆኑን ስናይ ‹‹የምትሉት ምን እንደሆነ አይቻለሁ ነገር ግን አንዳች ነገር ላደርግ አልችልም›› ብሎ ተናገረ፡፡ የቤተ መንግስቱን ጠባቂ ወታደሮች የተራ ለውጥ ሲያደርጉ የሚያሳዩትን ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት ይከታተሉ የነበሩ አገር ጉብኝዎች ወደ መናፈሻ ቦታዎቹ መመለስ ሲጀምሩ አጋጣሚውን ተጠቅመን ወደ መኪናችን ተቻኩለን ሄድን፡፡ እነዚያ ጥቃት ሊያደርሱብን የተዘጋጁት ግብረ ሰዶማውያን አንደኛውን ምልክታችንን ከመኪናችን ላይ ገንጥለውታል፡፡ሆኖም ባለቤቴ በሳጥን በሳጥን አድርጋ ከመኪናው ቻሲስ ጋር በብረት ሰንሰለት አስራው ስለ ነበር ከመኪናችን ውስጥ ያሉትን የታተሙ በራሪ ጽሑፎችን ከመኪናችን ውስጥ ማውጣት አልቻሉም፡፡ ፡፡

 http://www.emaso.org/pictures/clip_clip_image006.jpg 

በስቶኮልም ያሉ አንዳንድ ግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች ጣታቸውን እየቀሰሩ ደህና ሁኑ ይሉን ነበር፡፡ በአንደኛው ወጣት ካኔቴራ ላይ ‹‹ግብረ ሰዶማዊ ድርጊቶችን ለማድረግ የሚደፍር›› የሚል ትርጕም ያለው ቃል ይታያል፡፡ መኪናችን ውስጥ ገብተን ልንቀሳቀስ ስንል ጥቃት ሊያደርሱብን ሲሉ ያነሳናቸው ፎቶ ነው፡፡ በዚህ በበጋው ወቅት የስቶኮልም ፖሊስ የግብረ ሰዶማውያን ወንዶች /ጌይ/ ሰልፍ ላይ ለነርሱ ያለውን ድጋፍ ለመግለጥ የነርሱ መለያ ልብስ ለብሶ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ወጥቷል፡፡

ወደ ማረፊያ ሆቴላችን እየሄድን ሳለ በእንደነዚህ መሰል ክስተቶች ውስጥ ቀጥላ እንድትገባ የማልፈቅድ መሆኔንና አስቀድመን እንዳስታወቅነው በግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች ጥቃት ሊገጥሙን የሚችሉ ቦታዎች ላይ እንደማናቆም ለባለቤቴ ሐሳቤን ገለጽሁላት፡፡ እርሷ ግን መልሳ በእንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ እቅድን መለወጥ አንድም ለግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች ጥቃት እንደ መሸነፍ ድሉንም ለነርሱ እንደ መስጠት የሚቆጠር መሆኑን ገለጸችልኝ፡፡ ይህም ነገር የእነርሱን ጥቃቶች ፈርተው በነበሩ ሰዎች ሁሉ ላይ ደርሶአል፡፡ በእኛ ላይ እንደደረሰው አካላዊ ጥቃቶች፣ ማስፈራራቶች ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ /ኒዮ ፋሽሽት፣ ሆሞፎቢና የመሳሰሉት/ እያሉ ስም በማጥፋት ና የመተዳዳሪያ ሥራውን ወይንም የንግድ እንቅስቃሴውን በማውደም ጥቃት ሁሉ አድርሰዋል፡፡ ስለሆነም ሚስቴ በእቅዳችን መሠረት እንድፀና ፈለገች፡፡ እንዴት ያለች ሰልፈኛ መሆኗን ተመልከቱ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስለ ዛሬዎቹና ስለ ነገዎቹ ልጆች ፍላጎቶች ተቆርቋሪ፣ ግድ የሚላቸውን ና የሚጋፈጡ፣ ለግብረ ሰዶማዊነት የሕይወት የኑሮ ልምድ እንዳይዳረጉ የሚከላከሉ ሰዎች በሰዊድን እኛ ብቻ እንደሆንን ዓይነት ሰሜት ይሰማናል፡፡ እነዚሁ ምስኪን ልጆች ሌላ ድምፅ የላቸውም፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት ደጋፊዎች በሌላ በኩል እጅግ ጠንካራ የመገናኛ ብዙሃን ና የፖለቲካ ድምፅ አላቸው፡፡ እንደኛ ዓይነት በልጆች ጉዳይ ላይ ጥረቶችን የሚያደርጉ ሰዎችን ድርጅታቸው ለመስፋፋት የሚያደርገው ቀጣይ እቅድ ላይ ተፅዕኖ እንደምናደርስባቸው አድርገው እንደሚያዩን እንገነዘባለን፡፡ ከራሳቸው ባልተፈጠረ የጾታ ግራ መጋባት ምክንያት በስዊድን አገር በያመቱ ወደ ሁለት ሺህ ገደማ ወጣቶች የግብረ ሰዶማዊነት የኑሮ ልምምድን ይመርጣሉ፡፡

ሃሙስ ነሃሴ 31/2006 ቅሬታ

ዛሬ ምሽት ላይ በማዕከላዊ ስዊድን የምትገኘውን የእስኪልስቱና ከተማ ጎበኘን፡፡ እራታችን እየበላን ሳለ አንድ ወጣት ወደኛ መጣና የኛን ጽሑፎች እንድንሰጠው ጠየቀን፡፡ ከኛ ጋር ወደ ሕዝብ የመኪና ማቆሚያ እንዲከተለን ጠየቅነውና አብሮን ሄደ፡፡ ከመኪናችን ወጥቼ ሰላም ብዬ ልጨብጠው ስል እጄን ለመጨበጥ አልፈለገም፡፡ ነገር ግን የመሃላ ቃላትን እየደረደረ የኛን የማስተማሪያ መጽሐፍ እንጂ ሌላ የሚፈልገው አንዳች ነገር እንደሌለው ይነግረን ነበር፡፡ ወዲያውኑ ከወዴት እንደመጡ የማናውቃቸው ወጣት ልጆች እኛ ወዳለንበት አቅጣጫ መጡ፡፡ በኡሜ የተደረገውን ነገር እንዳይደገም በመፈለግ ደህና ሁኑ ብለን አካባቢውን ለቅቀን ሄድን፡፡ በስትሮን ግኖስ ባረፍንበት ሆቴል ስንደርስ በዚያኑ ምሽት የኛን የማስተማሪያ ጽሑፍ ለመውሰድ ከሆልስቶሃማር ወደ ኤልስኪልስቱና መጥቶ ከእኛ ጋር ሳይገኛን ከተማውን በመልቀቃችን ሳያገኘን ከቀረ ሰው የኢ-ሜይል መልእክት ደርሶን ነበር፡፡ ያሳዘነን ነገር ቢኖር እንዲህ ዓይነት መረጃ ፈልገው የሚመጡ ሰዎችን /ወላጆችን/ ሳንደርሳቸው መቅረታችንን ሲሆን ጨክነን ግን የተሻለ ዘዴ መፈለግ እንዳለብን ወስነናል፡፡ ያ ኢ-ሜይል ያደረገልን ሰው ድረ-ገጻችን ወደሌላ ቋንቋም መተርጐሙን ያውቅ ነበርና ምን ያህል እየሰራ (አክቲቭ) እንደሆነ ጠየቀን፡፡ ስመልስለትም ለዘላለም ብዬ መለስሁለት፡፡ በኤስኪልሲቱና የሚገኙ ከኤስ. ኤስ. ዩ. ድርጅት ሊሆን የሚችሉ ተቃዋሚዎች የራሳቸውን በራሪ ጽሑፍ እንደ ሰጡት ገልጾ ‹‹ምናልባት ስለናንተ በጎ ቃላት ላይኖራቸው ይችላል›› በማለት ገልጾልናል፡፡

ማክሰኞ ነሃሴ 29/2006 - በሆምሎቢዎች የደረሰብን ጥቃት

የኛ መልእክት ዓላማ ያደረገው ስዊድናውያን ወላጆች ቢሆንም በአር.ኤፍ.ኤፍ.ኤል. RFSL የተወከሉ ግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች ያላቸውን ሐይል ሁሉ በማሰባሰብ በኛ ና በሥራችን ላይ ጥቃት ለማድረስ አንቀሳቅሰዋል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት በድረ-ገጻቸው ላይ የሚያወጡትን መጥፎ የጾታ ግንኙነት መረጃና የስዊድን አገር ሰዎችን በሕግ የተከለከሉ አደንዛዥ እጾችን እንዲጠቀም የሰጡትን አስተያዬት በማጋለጣችን ሳይሆን እንደማይቀር እንገምታለን

ትላንት በኦገስ 28 በሰሜን ሰዊድን የምትገኘውን የኡሜን ከተማ ጎበኘን፡፡ ባለቤቴን ከኡሜ አውሮፕላን ማረፊያ ልቀበላት ሄጄ ነበር፡፡ ከኔ ጋር ለመሆን የተመለሰቸው በካሊፎርኒያ ከተማ የልጅ ልጆቻችንን ስትንከባከብ ቆይታ ከተለየችን ከሳምንት በኋላ ነበር ፡፡ ከአውሮፕላን ማረፊያው ወደ ማረፊያ ሆቴል እያሽከረከርን ስንሄድ በሚቀጥሉት ቀናት በጣም ሰላማዊና ዕረፍት የተሞላባቸው የጉዞ ቀናትን እጠብቃለሁ አልኳት፡፡ ግን በምሽቱ የሚጠብቀንን ነገር ከቶ አላወቅሁም፡፡ አጭር እረፍት ቆይታ እንደምናደርግበት ቀድመን እንዳስታወቅነው በኡሜ ከተማ መውጫ ላይ ወዳለው የማክዶናልድ ሴንተር ስንደርስ ያልተጠበቀ ብዙ ሕዝብ ተከማችቶ ጠበቀን፡፡ ካለፈው ተሞክሮአችን ተነስተን ሁኔታው ስንመለከተው የተሰባሰቡት ሰዎች ሁላቸውም ወላጆች ሳይሆኑ ያዘጋጀነውን የማስተማሪያ መጽሐፍት ፍላጎት ላላቸው ወላጆች እንዳናድላቸው ለመረበሽ የተሰበሰቡም ነበሩ፡፡ ጥላቻና ና ክፋትን ባህርይ ካደረባቸው ከእነዚህ ተቃዋሚዎች ምንም አልጠበቅንም፡፡ እራታችንን ከበላን በኋላ ከእነዚህ ሰዎች መካከል 30 ያህል ከሚሆኑት ጋር ተገኝተን ስንቶቹ ወላጆች መሆናቸውን ጠየቅናቸው ፡፡ አራት ወላጆች ብቻ አገኘን፡፡ እነርሱም መጥተው ያዘጋጀናቸውን ጽሑፎች ሰጥተናቸው የቀሩትን ሰዎች ትተን ለመሄድ ስንዘጋጅ ወዲያውኑ ግብረ ሰዶማውያን ወንዶች (ጌይ) ና የግብረ ሰዶማውያን መብት ተከራካሪዎች /ጌይና ጌይ አክቲቪስትስ/ ስለ ከበቡኝ ወደ መኪናዬ እንኳ መግባት አልቻልሁም፡፡ ቢሆንም የምችለውን ያህል ታግዬ ገባሁ፡፡ እቅዳቸው ከእነርሱ አንዳንዶቹ ወደ ተከፈተው መኪና ኋላ እንዳንገባ ና ሌሎቹ ደግሞ ያልተከፈቱትን ሳጥኖች ከፍተው መጽሐፍትንና ዲ.. ቪ. ዲዎችን ወደ መሬት ዘርግፈው በቁጣ በእግራቸው ረጋግጠው መስባበር ነበር፡፡ ልናደርገው የምንችለው ነገር ቢኖር ዝም ብለን ቆመን የሚሆነውን መመልከት ብቻ ነበር ፡፡ በእኔና በሚስቴ ላይ የተነሱ በግምት ከ20-30 የሚሆኑ ነበሩ፡፡ ይህንን ሁሉ ነገር ከፈጠሩ በኋላ ወዲያውኑ ሄዱ፡፡ የሞባይል ስልክ መያዜን አሳይቻቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን እነርሱ አድርጓል ብለው ሳይጠረጥሩኝ ባይቀሩም እኔ ግን ደውዬ ፖሊስ ፈጽሞ አልጠራሁም ፡፡ የተበታተነውን ሳይበላሽ የተረፈውን ነገር መልቀም ስንጀምር የእኛን ማቴሪያል ለመውሰድ መጥተው ከነበሩት ውስጥ አንዳንድ ደግ ወላጆች ባደረጉልን የሚደነቅ ድጋፍ መኪናችንን ካቆምንበት አካባቢ ለቅቀን ሄድን፡፡ ነገር ግን ተቃዋሚዎች እጅ ለእጅ በመያያዝ የሰው አጥር በመስራት መውጫ እስክናጣ ድረስ ከበቡን፡፡ ወደ እነርሱ አቅጣጫ ስናሽከረክር ደግሞ የድንጋይ ናዳ በማውረድ በመኪናዋ አካል ላይ በጣም ብዙ የቀለም መላላጥ አድረሰዋል፡፡ ፡

ይኼ ሁሉ ሲሆን አንድ የሬዲዮ ጋዜጠኛ በዚያ ነበረች፡፡ ልታነጋግረን ከቀረበችበት ቅጽበት ጀምሮ በሁሉ ነገሯ ከእነርሱ ጋር መወገኗን መናገር እንችላል፡፡ መድልዎና የጠላትነት አቋም ለሚታይበት የስዊድን የመገናኛ ብዙሃን ድርጅት (ማስ ሚዲያ) ቃለ መጠይቅ ላለመስጠት የነበረንን ዓላማ አጽንተን ቅር ቢላትም ከጋዜጠኛዋ ጋር ቃለ-ምልልስ ላለማድረግ ወሰንን፡፡ ያ ሁሉ ጥፋት ከደረሰብን በኋላ ጋዜጠኛዋ ባለቤቴን ስለሆነው ሁሉ ነገር የበኩሏን አስተያየት እንድትሰጣት በጠየቀች ጊዜ ባለቤቴ ‹‹የባሰ ነገር ሊሆንም ይችላል›› ብላ ባጭሩ መለሰችላት፡፡

በ ኡሚያ ከተፈጠረው ሁኔታ በኋላ ባለቤቴ ሰንሰለትና ቁልፎች ገዝታ የተረፉትን ዕቃዎች ለሌላ ቦታ መጠቀም እንድንችል ከመኪናው ፈሬም ጋር አያይዛ አሰረቻቸው፡፡

የግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች በሚቃወሟቸው ሰዎች ላይ ስለሚያደርሱት ጥቃት በበለጠ ማወቅ ከፈለጉ በአፈ ታሪክ 2 ነጥብ 7 ይመልከቱ፡፡ አሳዛኙ ነገር ግን በኛ ላይ ሆነ በመኪናችን ላይ የደረሰብን ነገር አይደለም፡፡ በእርግጥ የሚያሳዝነው ግን በመላው ስዊድን ተስፋፍቶ የሚታየው የሰዶማዊነት ባሕርይ ነው፡፡

ወደ ከተማዋ ከመድረሳችን ከሳምንት በፊት በከተማዋ የአካባቢው ጋዜጣ /ቤስተርቦተን ኩሪረን/ ለአራት ቀናት /ረቡዕ፣ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ/ ተከታታይ የማስተዋወቅ ስራ ሰርተን ነበር፡፡ ሐሙስ ዕለት ከጋዜጣው አዘጋጆች ተደውሎ የመጨረሻዎቹን ሁለቱን ቀናት የማስተዋወቁን ሥራ እንሠርዛለን ብለው ደወሉልኝ፡፡ ጫና ደርሶባችሁ ነወይ ብዬ ስጠይቃቸው በአዎንታ መለሱልኝ፡፡ ትናንት ማታ ከማክዶናልድ ሬስቶራንት ስወጣ ማስታወቂያውን ማቋረጥ ለምን እንደፈለጉ ልገነዘብ ችያለሁ፡፡ በአንዲት ትንሽ የአካባቢ እለታዊ ጋዜጣ ላይ ታላቅ ጥፋት ማድረስ ለግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች /ሆሞሴክሽዋል ሎቢ/ብዙ የሚያደክም ነገር እንዳይደለ መገንዘብ አያቅትም፡፡ በሂደቱ በስዊድን አገር ያለው ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ሌላ አደጋ እየገጠመው እንደሆነ ያመለክታል፡፡

አንድ ሰው ድርጊቱን ለፖሊስ ሪፖርት እንድናደርግ ሐሳብ ሰጥቶናል፡፡ ነገር ግን በልብህ ስለርሱ ርኅራኄ ስለሚሰማህ ሰው ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ እጅግ ከባድ ነው፡፡ የግብረ ሰዶማውያን ደጋፊዎች (ሆሞሎቢ) ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ የኛ ጠላቶች አይደሉም፡፡ ለሌሎቹ የሰው ልጆች እንደምናደርገው ለእነርሱም ግድ ይለናል፡፡ እንደዚሁም ወላጆች ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው የወደፊት የፆታ ግንዛቤ ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር እንዲችሉ አስፈላጊውን ኢንፎርሜሽን መስጠት እጅግ ጠቀሜታ አለው፡፡

ቅዳሜ ነሃሴ 26/2006 የቃለ መጠይቆች መሠረዝ
ውድ ወዳጆቼ

በስዊድን የሰዓት ኦአቆጣጠር ቅዳሜ እኩለ ሌሊት ነበር፡፡

ከባለቤቴ ጋር በስልክ ስናወራ ለናንተ ከስዊድን ሰላምታ እንድልክ ሐሳብ አቀረበችልኝ፡፡ በስዊድን አገር ካደረግነው ጉዞ የተነሣ አሁን ያነሳችልኝ ጉዳይ ተገቢና ወቅታዊ ነበር /ከመልክዐ ምድራዊ አነጋገር/ እኔ አሁን ያለሁት ሃፓራንዳ /ፊንላንድ/ ነው፡፡ ወደ ሰሜን በተጓዛችሁ ጊዜ ጫፍ ላይ የምታገኙት ቦታ ነው፡፡

በዚህ የስዊድን ሰሜናዊ ክፍል በጣም ብዙ ህዝብ የሚኖርበትና አብዛኛውም ኢኮኖሚ ሥራዎች የሚሠሩበትም ቦታ ከቦልቲክ ባህር ጋር በሚያዋስነው የምሥራቅ የባህር ዳርቻ ነው፡፡ ሀፓራንዳም በሰሜን ጫፍ የምትገኝ ቦታ ስትሆን ምንም እንኳ የድንበሩ ጫፍ ከዚያ ትንሽ እልፍ የሚል ቢሆንም ከፊንላንድ ጋር አዋሳኝ ድንበር ነው፡፡ በዚህ የሰሜን ጫፍ ከሰኔ አጋማሽ እስከ ሐምሌ መጀመሪያ ባሉት የዓመቱ ወቅቶች ፀሐይ ፈጽሞ አትጠልቅም፡፡ ምሽቱ ጨለምለም ያለ ቢሆንም ፈጽሞ ግን አይጨልምም ከጥቂት ወራቶች በኋላ በጣም ጨለማ ይሆንና ቀናቱ ደግሞ አጭር ይሆናሉ፡፡

ትንሽ ልጅ በነበርሁ ጊዜ ከሰሜን ሀፓራንዳ ጫፍ እስከ ይስታድ ደቡብ ጫፍ በብስክሌት የሄደ በአካባቢው ሕዝብ ዘንድ የታወቀና የተከበረ ‹‹ስቶልፋርፋር›› /‹‹ከብረት የተሠራ አያት››/ የሚባል ሰው ነበር፡፡ በሌላ በኩል እኔ ራሴ ዛሬም እንደማደርገው በሀፓራንዳ ብስክሌት እጋልባለሁ፡፡ ከሦስት ሳምንት በኋላ ደግሞ በይስታድ እጋልባለሁ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የብስኪሌት ጉዞ ለተመሳሳይ ጽናትና ጉልበት መገለጫነት ብቃት የለውም፡፡ የሚኒባሳችን የመካከለኛውን ወንበር አጥፌ ብስኪሌቴን ጭኜ አምጥቻለሁ፡፡ በዛሬው የብስኪሌት ጉዞዬ ሰውነቴን ዘና አድርጌ ጉልበቴ ላይ ያለውን ሕመሜን ታገሼ በመንቀሳቀሴ የአካል ህከምና (ፊዚካ ቴራፒሰት) ሃኪሜን ያስደትልኛል፡፡ መኪናዬን እየነዳሁ ወደ ፊንላንድ ድንበር ሄድሁ ሆኖም ከድንበሩን በፊት ያለውን የመጨረሻ መውጫ ልብ ሳልለው ቀረሁ፡፡ አማራጭም ስላልነበረኝ ዝም ብዬ ቀጠልሁ፡፡ የጉምሩክ ፍተሻው ቢሮ ስደርስ ሳላውቀው በድንገት ከሚገባኝ በላይ አልፌ ሄጃለሁና መመለስ ፈልጌያለሁ ብዬ ልነግራቸው ባለስልጣኖችን ፈለግሁ ፡፡ ነገር ግን በዚያ በቅዳሜ አኩለ ሌሊት አንድም ሰው ላገኝ አልቻልሁ፡፡ በጊዜው ብዙም የንግድ ተሽከርካሪዎች ባለመኖራቸው እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሄዷል፡፡ ተመልሼ ወደ ፊንላንድ ጉዞዬን ቀጠልሁ፡፡ ባረፍሁበት ሆቴል ፓስፖርቴን ትቼ በመምጣቴ ችግር ላይ ልወድቅ እንደምችል ተከሰተልኝ፡፡ ከዚያም በሌላ አቅጣጫ ብመለስም በዚያም በሄድሁበት መንገድ አንድም ሰው አልነበረም፡፡ ከ10 ዓመት በፊት እንደሄድንባቸው እንደጎበኘኋቸው አገሮች ለምሳሌ /እስራኤልና ግብፅ ፣ እስራኤልና ዮርዳኖስ፣ ግሪክና ቱርክ ጋር ሲነጻጸር እንዴት ያለ ልዩነት ነው፡፡

ስለ ጉዞ ምክንያታችን እናንሣ፡፡ ነገሩ ደህና እየሄደ ነው፡፡ ያለፈውን ምሽት ያሳለፍሁት በፒቴ ነው፡፡ በከተማው ውስጥ እያሽከረከርሁ ሳለሁ በአንድ ሕንፃ አጠገብ ሳልፍ በሕንጻው ላይ ‹‹አር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. ኖርድ›› የሚል ጽሑፍ አየሁ፡፡ ይህም ደርጅት በስዊድን መንግሥት ከፍተኛ የፋይናንስ ድጎማ የሚደረግለት ግብረ ሰዶማዊነትን የሚደግፍ ድርጅት ነው፡፡ በትናንትናው ምሽት እዚያው ፒቴ ከተማ ባለው የከተማይቱ ሆቴል /ስታድስ ሆቴሌት/ አሰሳ ሳደርግ በ20ዎቹና በ30ዎቹ ዕድሜ ክልል የሚገኙ በመካላላቸውም በነርሱ ዕድሜ ደረጃ የሆኑ ሴቶች የማይታዩበት የበርካታ ወንዶች ስብስብ አየሁ፡፡ ዕድሜያቸው ወደ 15 ዓመት ገደማ የሚመስሉ 3 ወንዶች ልጆችን አየሁ፡፡ ወላጆቻቸው አብረዋቸው ያሉ አይመስሉም፡፡ ዛሬ ጠዋት ሆቴሉን ለቅቄ ያዘጋጀነውን የማስተማሪያ መጽሐፍንና ዲ.ቪ.ዲዎችን ወደ ምናድልበትና በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያላቸውን ወላጆች ሁሉ ለማነጋገር እንገኛለን ብለን ባስተዋወቅነው እዚያው ‹‹ፒቴ›› በሚገኘው በቤንዚን ማደያው ተገኘን፡፡ የኛ ዓላማ አያቶችን፣ ወላጆችን መድረስ ነው እንጂ ግብረ ሰዶማውያን ወንዶችና ሴቶችን አይደለም፡፡ ነገሩን ስንፈጽም የምናደርገው እንዲህ ነው፡፡ በማስታወቂያ በገለጽነው መሰረት ለመኪናችን ነዳጅ ለመቅዳት ና ለሆዳችን የሚያስፈልገንን ለማግኘት የቤንዚን ማደያ ወይም አንድ ምግብ ቤት እንሄዳን፡፡ ምክንያቱም የቦታው ባለቤቶች ላይ ቅር እያላቸው ስለሄደ ያመጣናቸው ጽሑፎችና ሌሎች ነገሮች በቆምንበት ቦታ ማደሉን አንፈልገውም፡፡ ስለሆነም ሰዎች ከሚበሳጩብን የቤንዚን ማደያውን ሆነ ሆቴሉን ለቅቀን መኪናችን በጎንና በጎን በትላልቅ ፊደል የተጻፉ www.Amoso.org. የሚል ምልክት ስላለው በቅርብ ወደሚገኘው የአካባቢው የሕዝብ ስፍራ እንሄድና ሊያገኘን ፈልጎ ይከታተለን ለነበረውም ሆነ የምናድለው ጽሑፋችን የሚፈልገውን ሁሉ በዚያ እንገኛለን፡፡

የአር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. ማዕከል ባለበት በፒቲያ ከተማ ዛሬ በኛ ላይ የደረሰው ነገር ቀድሞ የተገመተ ነበር፡፡ ጥቂት የተበሳጩና የተናደዱ ሰዎች ተሰብሰበው ይጠብቁኝ ነበር፡፡ የነዳጅ ማደያው ባለቤት ራቅ ብለው እንዲጠብቁ ነግሮአቸው ስለነበር ነዳጅ ቀዳሁ፡፡ በአንደ ጥግ ወደሚገኝ አንድ የሕዝብ ማዕከል ቦታ እየነዳሁ ሄድሁ፡፡ አንድ ብልህ ሴት ወደኔ መጥታ በድረ-ገጹ ላይ ስላነበበችው ጉዳይ ተጨማሪ ጽሑፍ ከእጄ በመውሰዷ ተደስታ ነበር፡፡ ለጓደኞቿም ተጨማሪ ጽሑፎች ጠየቀችና ሰጠኋት፡፡ ከዚያ ቀጥሎ አንድ ጋዜጠኛ ከፎቶግራፍ አንሺው ጋር መጣ፡፡ ከኔ ጋር ቃለ ምልልስ ማድረግ ፈለገ፡፡ በ‹‹ሼሌፍቴ›› ከአንድ ምሽት በፊት ቃለ ምልልስ እንደማደርግ ተናግሬ ነበር፡፡ በጣም ደግና ትሁት የሆኑ እንደ ቆንጆ ወጣት ወንድ ና ኮረዳ ቀረቡኝ፡፡ ለራሴም ሆነ ለባለቤቴ በዚህኛው ጉዞአችን ወቅት አንድም ቃለ ምልልስ ማድረግ እንደማልፈልግ የተናገርሁ ብሆንም ግን በዚህ ጊዜ ለማድረግ መስማማት እንዳለብኝ አሰብሁ፡፡በኋላ ግን በእቅዴ ባለመጽናቴ ተጸጽቻለሁ፡፡ ወጣቷ ኮረዳ ወዲያውኑ እንዲህ አለችኝ፡- እኔ ግብረ ሰዶማዊት ነኝ /‹‹ሌስቢያን››/ ከቤተሰቤ ደግሞ ታናሿ ሴት እኔ ነኝ እንዴት ሌስቢያን እንደሆንሁ ልታስረዳኝ ትችላለህ ወይ? ብላ ቀጥላም እርሷ ጉዲፈቻዎችን ተቀብላ ብታሳድግ እነርሱም ደግሞ ሌዝቢያን ይሆናሉ ወይ ብላ ጠየቀችኝ፡፡ እርሷ በጣም ተሟጋች ነች፡፡ ሌላው ደግሞ ለኔ ድረ-ገጽ ይዘትና ከቶ እውቀቱ የሌላቸውና እኔን ለመሰማት ፈቃደኛ ያልነበሩ ነበሩ፡፡ እኔ ደግሞ የማልፈልገው ዋና ነገር ይኸ ነው፡፡ ጉዞአችንም ሆነ ድረ-ገጻችንም የሚናገረው ስለዚሁ ሁዳይ ነው፡፡ እኛ ልንደርሳቸው የምንፈልገው አድማጮች ወላጆች እንጂ ግብረ ሰዶማውያን አይደለም፡፡ በሚጽፏቸው ታሪኮች ውስጥ የሚናገሯቸውን አሉታዊና መድልዋዊ ቃላት አውቃለሁ፡፡

ከዚያ ደግሞ ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ ላደርገው የነበረውን ቃለ ምልልስ ሠረዝሁት፡፡ በአሜሪካ ‹‹አንድ ጊዜ ሲያታልሉህ ነውሩ በነርሱ ላይ ይሆናል፡፡ ሁለተኛ ጊዜ ሲያታልሉት ግን ነውሩ ባንተ ላይ ይሆናል›› የሚል ተረት አለ ብዬ ነግሬው አልተገኘሁለትም፡፡ ይሁን እንጂ ከጋዜጠኛው ጋር በተገናኘንበት በዚያች አጭር ቅጽበት ፎቶግራፍ አንሺው በትንሹ አርባ ጊዜ አንስቶኛል፡፡ በድረ-ገጻችን የመገናኛ መሰመር በኩል የአካባቢው የሬዲዮ ጣቢያዎችና የጋዜጣ ደርጅቶች በርካታ የቃለ ምልልስ ጥያቄዎች አቅርበውልኝ ነበር፡፡ ሆኖም ጊዜ ቢኖረኝ ቃለ ምልልሱን እንደማደርግ በትህትና ገልጨላቸው መልሼላቸዋለሁ፡፡ በእኔ እምነት የግብረ ሰዶማውያን ማኅበረሰብ /ጌይ ኮሚዩኒቲውን/ የሚያበሳጨው ዋና ምክንያት በአፈ ታሪክ አንድ ላይ ስላነሣነው ስለ ሁለቱም የሕይወት ዘይቤዎች ተፈላጊነት አተያየታቸው ጋር መያያዙ ነው፡፡ በሁለቱ የአኗኗር ዘይቤዎች ያለውን ከፍተኛ ልዩነት ለማሳየትና ወላጆች ልጆቻቸው ወደ ጉርምስና ሲደርሱ የግብረ ሰዶማዊነትን ዝንባሌ እንዲያስወግዱ የአር.ኤፍ.ኤስ.ኤል (RFSL) ድረ-ገጽ በፆታዊ ግንኙነት ዙሪያ የሚያወጣቸውን ከፍተኛ የብልግና ይዘታቸው ያላቸውን ማቴሪያሎች እንጠቀማለን፡፡ ስለምንናገረው ነገር ተጨማሪ አስተያየት ማወቅ ከፈለጉ ምን ስዊድንኛ ቋንቋ ባይችሉም (www.amaso.org) ድረ-ገጽ ከፍተው አፈ-ታሪክ 1 በሚለው ርእስ ስር ሰባት ገጾችን ወደ ታች ፈልገው ማጣቀሻ. 4 የሚለውን ማገናኛ ቢጫኑ አር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. ለአንባቢዎቹ ስለ ሕጋዊ ያልሆኑ አደንዛዥ እጾችን አጠቃቀም የሰጠውን አስተያየት ማንበብ ይችላሉ፡፡ ከዚያ ቀጥለው ማጣቀሻ. 5 ቢመለከቱ ድረ ገፃቸው የቱን ያህል አሳፋሪ ይዘቶች ባሏቸው ነገሮች የተሞላ መሆኑን ይገነዘባሉ፡፡ ይህም ሁኔታ አር.ኤፍ.ኤስ.ኤልን ግራ አጋብቶታል፡፡ በአንድ በኩል ይህንን የማይመች ይዘት ያለውን ነገር በማጋለጣችን ሊያጠቁን ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ በኩል ጉዳዩ በሕዝቡ ዘንድ እንዲታወቅባቸው አይፈልጉም፡፡

ከትናንት በስቲያ በሰሜን ስዊድን ትልቁ ከተማ በሆነው በኡሚያ ከተማ ከሚታተም ዋና ጋዜጣ /ቤስተርቦተን ኩሪረን/ ኤዲቶሪያ ቦርድ አባል ጋር በጣም ደስ የሚያሰኝ ጭውውት አድርጌ ነበር፡፡ በዚያን ዕለት ጧት ከሪፖርተሮቻቸው አንዱ ደውሎልኝ በጋዜጣው ላይ እንዲታተሙ ከተስማማባቸው አራት ማስታወቂያዎች ሁለቱን ብቻ ካወጡ በኋላ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ቀሪው ሥራ እንዲሠረዝ ማዘዛቸውን ነገረኝ፡፡ በዚያኑ ቀን ከሰዓት በኋላ ደግሞ ይኸው ሰው በሞባይል ስልኬ ላይ ደውሎ በመኪናዬ ውስጥ ግማሽ ሰዓት ገደማ አወራን፡፡ አንደገና ደግሞ ደውሎ ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ግንዛቤ/ዕውቀት ለማግኘት እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ ስለኔ ሳይሆን ስለ ጉዳዩ ብዙ ማወቅ ፈልጎ ነው፡፡ ያንን ወድጄለታለሁ፡፡ በድርጅቱ አስተዳደራዊ መዋቅር ተዋረድ ሁለተኛ ሰው እንደነበረና ለምን የማስታወቂያ ሥራ እንዲሠረዝ እንደ ተደረገ አለቃውን ለማነጋገር ፈልጎ ያለመቻሉን ገልጾ ከኔ ሊሰማ ወደደ፡፡ ጉዳዩ መሠረዙን በመስማቱ መገረሙን ነግሮኛል፡፡ የኢዲቶሪያል ቦርድ አባላት ፈቃደኛነታቸው ከታወቀ ወደ ጋዜጣው ቢሮ መጥቶ ስለ ጉዳዩ ልንነጋገር እንደምችል ሊነግረኝ እንደፈለገ ገለፀልኝ፡፡ አንድም ጋዜጠኛ ቃለ ምልልስ ጥያቄ ያቀረበልኝ አልነበረም፡፡ ከዚያ ሁኔታ ምን ሊወጣ እንደሚቻል እናያለን፡፡ ይህንን እንዳደርግ የገፋፋኝን ምክንያት ማወቅ ፈልጓል፡፡ የስዊድን አገር የወደፊት ትውልድ በተመለከተ ባለቤቴና እኔ ግድ ስለሚለን መሆኑን ገለጽሁለት፡፡ በስዊድን አገር በያመቱ ከ1000-2000 የሚሆኑ ወጣት ወንዶች በግብረ ሰዶማዊነትን የአኗኗር ዓይነትና ከእርሱ ጋር በተያያዘ ሥቃይ እንደሚሳቡ የታወቀ ነው፡፡ በዚህ አስደንጋጭና አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ቀዳዳ መፍጠር መቻሉ ሕይወታችን ከንቱ እንዳልደከምን ያመለክታል፡፡ ነገሩ እንደታቀደው እንዳይፈጸም በማድረግ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ እንደ ተወጣን ይሰማናል፡፡ ካንተ በላይ በሆነ ታላቅ ሁኔታ ውስጥ ባለ ድርሻ መሆንና ከራስ ይልቅ ሌላን የአገርህ ሰው ሊጠቅም በሚቸል ነገር መሳተፍ በርግጥ በጣም የሚያነቃቃ ነገር ነው፡፡

በምንመራው በየትኛውም የህይወት መስመር እውነት ለሁልጊዜም በዓመፃ ከቶ አይጨፈለቅም፡፡ በመጨረሻው እውነት አሸንፋ ልትወጣ ይገባል፡፡ ኤች ሲ አንደርሰን የደንማርክ ተረት-ተራች ‹‹ዘ ኢምፐረርስ ኒው ክሎዝ›› በተባለው ተረት መጽሃፍ እንደገለጸው አንዳንዴ አንዳንድ ነገር በፍጥነትና በድንገት ይሆናል፡፡ ታናሽይቱ ልጅ ንጉሠ ነገሥቱ ልብስ የላቸውም›› ብላ በጮኸች ጊዜ ወዲያውኑ እያንዳንዱ ሰው ንጉሠ ነገሥቱ እንዴት ልብስ እንዳልለበሱ ማየት ችሏል፡፡ ነገር ግን ግብረ ሰዶማዊነት ስረ መሰረት በውርስ የሚተላለፍ /ሄሬዲተሪ/ እንደሆነ የሚነገረው ትልቅ ውሸት በሳይንሳዊ መረጃ ክብደት ውድቅ እስከሚሆንበት የመጨረሻ ጊዜ ድረስ የትውልድን አብዛኛው ዘመን ሊፈጅ ይችላል፡፡ የአገር የሕዝብ አቀራረብና አመለካከት እየተለወጠ የሚሄደው በቀስታ ና በአዝጋሚ ሂደት ውስጥ ነው፡፡

ትልቁ ሥዕል ይህን ይመስላል፡፡ ከ1960ዎቹና ከዚያም በፊት ባሉ ዓመታት ሰዎች ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ብዙም አያወሩም ነበር፡፡ አቤት ነገሮች እንዴት ተለዋውጠዋል !!! ነገር ግን ያን ዘመን የነበሩ ሳይኪያትሪስቶችና ሳይኮሎጅስቶች የችግሩ ሥረ መሠረት ልጆች ከአባቶቻቸው ጋር የነበራቸው ግንኙነት ማነስ እንደ ነበር ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ በአፈ ታሪክ 2 ላይ እንደገለጽሁት ስለ ሁኔታው ቀድሞ የተገነዘበው ቤበር ብቻ አልነበረም፡፡ ነገር ግን የ1970ዎቹን የፆታዊ አብዮትና ግብረ ሰዶማውያን ሰዎች ሁለቱን ታላላቅ የአሜሪካ ድርጅቶች /የሳይካትሪስትና የሳይኮሎጅ ኢንስቲቲዩትስ/ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ግብረ ሰዶማዊነትን ያመጣል ተብሎ የሚታሰበው ዘረ-መል (ጅን) በመፈለግ ረገድ እጅግ ሰፊ የሆነ የጥናት ግፊት ቀጠለ፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት በውርስ የሚተላለፍ እንደሆነ ማረጋገጫ መስጠቱ ግብረ ሰዶማውያን ሰዎች ሁሉ ዓለም አቀፍ እውቅናና ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ ምን ሊሆን እንደሚችል ገምቱ፡፡ ግብረ ሰዶማዊ የሚያደርግ ዘረ-መል (ጅን) እስካሁን አልተገኘም፡፡ ያ ብቻ አይደለም ያለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ የተደረጉ የምርምር ሥራዎች ግብረ ሰዶማዊ የሚደርግ ዘረ-መል (ጅን) ልናገኘው የማንችል መሆኑን ማሳየታቸው ነገሩን ምሥጢራዊ /እንቆቅልሽ/ ያደርገዋል፡፡ የጥናቱም ውጤት በውርስ ሊተላለፍ የማይችል እንደሆነ ነው ያረጋገጠው፡፡ ይህን ሐቅ ለመረዳት የሚያስችለው ቁልፍ በአንድ ዓይነቶች መንትዮች የተደረጉ ጥናቶች ናቸው፡፡ ያ ደግሞ ዋነኛ ቁልፍ ነው፡፡ የቤይሊ-ዱን-ማርቲንና ቤይበር-ብሩክነት ጥናቶች ያመለከቱት የፒ.ሲ. እሴት/ፕሮባንድ ኮንኮርዳንት/ 11%ና 7% እንደሆነ ነው፡፡ አማካዩን 9% እንውሰድ እንበል፡፡ ይህም የሚያመለክቱት ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ መንታ ግብረ ሰዶማዊ የመሆን እድሉ 9% ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ግብረ ሰዶማዊ የሚያደርግ ዘረ-መል (ጅን) ቢኖር ኖሮ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ ቁጥር 100% ይሆንና በእውነታነቱ ትንሸ አነስ ብሎ ሊታይ ይችል ነበር፣ ምክንያቱም የልከት ሥራዎች (measurements) ዙሪያ ስህተት የሚከሰትባቸው ሁኔታዎች መቼም ስለሚኖሩ ነው፡፡ ይኸው 9%ም ቢሆን ከ2-4% ሁሉም ወንዶች ግብረ ሰዶማውያን ይሆናሉ ከሚለው በጣም የሚበልጥ ቁጥር ነው፡፡ በተመሳሳይ አባትና ተመሳሳይ ሁኔታዎች ውስጥ የማሳደጉን ሁኔታ ግምት ውስጥ ብናስገባ ቁጥሩ ከተገመተው ከ2-4% በላይ ይሆናል፡፡ አስተውሉ 9% ማለት ተመሳሳይ መንትያ ውስጥ ሌላው ግብረ ሰዶማዊ ለመሆን 9% ዕድል አለው ማለት አይደለም፡፡ ያም ቁጥር አሁንም ቢሆን ከጠቅላላው ሕዝብ አንጻር ከ2-4% ነው፡፡

አሁን ልክ እኔ እንደ ደከመኝ ደክሟችሁ ይሆናል፡፡